ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, November 14, 2013

የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ በኖርዌይ (Ethiopian Community in Norway) በሳውዲ አረብያ የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው ሰቆቃ ያዘጋጀው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ


የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ በኖርዌይ (Ethiopian Community in Norway) ዛሬ ህዳር 5/2006 ዓም በሳውዲ አረብያ የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው ሰቆቃ ያዘጋጀው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ቁጥሩ  ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት በኖርዌይ ዋና ከተማ በኦስሎ በሚገኘው የሳውዲ አረብያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተካሄደ።


ከቀትር በኃላ  በ10 ሰዓት የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ  በርካታ ወጣቶች፣ በእድሜ የገፉ አረጋውያን እና እድሜያቸው  ከአንድ ዓመት ያልዘለሉ ሕፃንትን የያዙ እናቶች ሁሉ የታደሙበት ነበር።እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ በቆየው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ -

- የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች እና ሲቪክ ማህበራት ተወካዮች አጫጭር ንግግሮች አድርገዋል፣

- የሳውዲ አረብያ መንግስት በሀገሩ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰውን በደል የሚያጋልጡ በማህበራዊ ድህረ ገፆች የተለቀቁት ፎቶዎች በትልቁ ታትመው እንዲታዩ ተደርገዋል፣

- የተለያዩ መፈክሮች ተሰምተዋል፣

-  ለሳውዲ አረብያ ኢምባሲ የተዘጋጀው የተቃውሞ ደብዳቤ ተሰጥቷል፣

-  የሳውዲ አረብያ መንግስት ንጉሳውያን ቤተሰቦች የያዘ ፎቶግራፍን  እንዲቃጠል በማድረግ ሰልፈኛው ተቃውሞውን ከመግለጡም በላይ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በቸልታ እና ተገቢውን የዲፕሎማቲክ ግንኙነትን ያልጠበቀ አያይዝ ኢትዮጵያውያኑን በእጅጉ አስቆጥቷቸዋል። በሰልፉ ላይ ከተነገሩት ንግግሮች ውስጥ የኢህአዲግ ወያኔ መንግስት ለዜጎቹ የሚሰጠው ዋጋ በእጅጉ ያነሰ መሆኑ በተደጋጋሚ ከመወሳቱም በላይ አንድ ተናጋሪ '' ዛሬ ወገኖቻችን ሥራ ፍለጋ በእየ አረብ ሃገራቱ የሚሰደዱት ከ 40 ቢልዮን ብር በላይ በመዘረፉ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ለእዚህም ተጠያቂው እራሱ ወያኔ ነው'' በማለት በምሬት ተናግረዋል።

በመጨረሻም  በሰሞኑ የሳውዲ ፖሊስ እና ወጣቶች  ተግባር የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን  ፎቶ ሰልፈኛው ''ስራቸውን ይመልከቱት በማለት ኢምባሲው አጥር ላይ እንዲቀመጥ ከተደረገ በኃላ የሰልፉ ስነ ስርዓት ፍፃሜ ሆኗል።

የሰልፉን ገፅታ በከፊል የሚያሳየውን ፎቶ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።














No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።